1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአሜሪካንን ጫና የተቃወሙ ሰልፎች በጀርመን ከተሞች

ዓርብ፣ ኅዳር 24 2014

በዋና ከተማ በርሊን ፣በንግድ ከተማዋ በፍራንክፈርትና የተመድ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት በሚገኝበት በቦን ከተሞች በተካሄዱት ሰልፎች ላይ የተካፈሉት የኢትዮጵያን ህልውና ይፈታተናል ያሉትን የውጭና የሀገር ውስጥ እንቅስቃሴም ተቃውመዋል። በተለይ ፍራንክፈርት ውስጥ የኢትዮጵያ መንግሥትን የሚያወግዝ ሌላ የአደባባይ ሰልፍም ተደርጓል። 

https://p.dw.com/p/43oNL
Deutschland | Äthiopier demonstrieren in Frankfurt
ምስል Endalkachew Fekade/DW

የአሜሪካንን ጫና የተቃወሙ ሰልፎች በጀርመንን ከተሞች

በሦስት የጀርመን ከተሞች ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያን ትውልደ ኢትዮጵያውያን ኤርትራውያን  እንዲሁም የኢትዮጵያ ወዳጆች ምዕራባውያን ሀገራት በተለይ ዩናይትድ ስቴትስ በኢትዮጵያ ላይ ታሳድራለች ያሉትን ግፊትና ጫና እንዲሁም ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሀን ያሰራጫሉ ያሏቸውን የሀሰት ዜና በመቃወም ሰላማዊ ሰልፎች አካሄዱ። በዋና ከተማ በርሊን ፣በንግድ ከተማዋ በፍራንክፈርትና የተመድ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት በሚገኝበት በቦን ከተሞች በተካሄዱት ሰልፎች ላይ የተካፈሉት፣ የኢትዮጵያን ህልውና ይፈታተናል ያሉትን የውጭና የሀገር ውስጥ እንቅስቃሴም ተቃውመዋል። በተለይ ፍራንክፈርት ውስጥ የኢትዮጵያ መንግሥትን የሚያወግዝ ሌላ የአደባባይ ሰልፍ መደረጉን እንዳልካቸው ፈቃደ  ዘግቧል። 

Deutschland NoMOre Demo in Bonn
ምስል Mantegaftot Sileshi Siyoum/DW

እንዳልካቸው ፈቃደ
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ