1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

  የያማሞቶ ጉብኝት

ሐሙስ፣ ሚያዝያ 18 2010

አንድ የፖለቲካ ተንታኝ እንዳሉት ደግሞ የያማሞቶ የአፍሪቃ ቀንድ ጉብኝት ኃያላኑ መንግሥታት አካባቢዉን ለመቆጣጠር የሚያደርጉት ሽሚያ አካል ነዉ።

https://p.dw.com/p/2wjsq
USA Washington - Donald Yamamoto (L)
ምስል picture-alliance/dpa/J. Lo Scalzo

 

የዩናይትድ ስቴትሱ የአፍሪቃ ጉዳይ ረዳት ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር አምባሳደር ዶናልድ ያያማሞቶ በአፍሪቃ ቀንድ ሐገራት የሚያደርጉትን ጉብኝት እንደቀጠሉ ነዉ።ያማማቶ በጀብቲ እና ኤርትራ ያደረጉትን ጉብኝት አጠናቅቀዉ ዛሬ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ የዩናይትድ ስቴትስ ዉጪ ጉዳይ መስሪያ ቤት ቃል አቀባይ አስታዉቀዋል።ቃል አቀባይዋ አክለዉ እንዳሉት ያማሞቶ ከኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ጋር የሁለቱን ሐገራት ግንኙነት እና ያካባቢዉን ሠላም አንስተዉ ይነጋገራሉ።አንድ የፖለቲካ ተንታኝ እንዳሉት ደግሞ የያማሞቶ የአፍሪቃ ቀንድ ጉብኝት ኃያላኑ መንግሥታት አካባቢዉን ለመቆጣጠር የሚያደርጉት ሽሚያ አካል ነዉ። 

መክብብ ሸዋ

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሰ