1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጀርመን ም/ቤት የኢትዮጵያና ኤርትራን መቀራረብ አወደሰ

ዓርብ፣ ጥር 10 2011

ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ታሪካዊ የሰላም ስምምነት ከፈፀሙ ከመንፈቅ በኋላ የጀርመን ምክር ቤት ሁለቱ የምስራቅ አፍሪቃ ሃገራት ያሳዩትን ሰላማዊ ቅርርብ አወደሰ። ምክር ቤቱ ሐሙስ ምሽት ባካሄደው ስብሰባ በጠላትነት ይተያዩ የነበሩት ተጎራባቾቹ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ሰላም ለማስፈን የፈፀሙት ዉል ዋንኛ ርምጃ ነዉ ሲል አድንቋል።

https://p.dw.com/p/3BnjY
Feierstunde 100 Jahre Frauenwahlrecht im Bundestag
ምስል picture-alliance/dpa/B. von Jutrczenka

የምክር ቤት አባላቱ በኤርትራ የዴሞክራሲ ግንባታን ፈር እንዲቀድ ጠይቀዋል

ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ታሪካዊ የሰላም ስምምነት ከፈፀሙ ከመንፈቅ በኋላ የጀርመን ምክር ቤት ሁለቱ የምስራቅ አፍሪቃ ሃገራት ያሳዩትን ሰላማዊ ቅርርብ አወደሰ። ምክር ቤቱ ትላንት ሐሙስ ምሽት ባካሄደው ስብሰባ በጠላትነት ይተያዩ የነበሩት ተጎራባቾቹ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ባለፈዉ የጎርጎሮሳዊዉ 2018 ዓመት በመካከላቸዉ ያለዉን ዉዝግብ ለማስወገድና ሰላም ለማስፈን የፈፀሙት ዉል ዋንኛ ርምጃ ነዉ ሲል አድንቋል። ሁለቱ ሃገሮች ኤርትራ በጎርጎረሳዉያኑ 1993 ዓ.ም. ነፃነትዋን እስክታገኝ ድረስ አንድ እንደነበሩ የጀርመኑ የዜና ወኪል «DPA» በዘገባዉ አስታዉስዋል። ኤርትራ ነፃነትዋን ከአገኘች ከአምስት ዓመት በኋላ በኢትዮጵያ እና ኤርትራ መካከል በተቀሰቀሰዉ ጦርነት በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መሞታቸዉን የጀርመኑ የዜና ወኪል ዘግቦአል። የጀርመን ምክር ቤት ትናንት ሃሙስ ምሽት ባደረገዉ ስብሰባ ላይ የኢትዮጵያ መንግሥት የጀመረዉን የለዉጥ ተሃድሶ እንዲቀጥልበት አበረታቶአል። ይህንኑ ተከትሎ የምክር ቤቱ አባላት የኤርትራ መንግሥት በሃገሪቱ የዴሞክራሲ ግንባታን ፈር እንዲቀድ ጠይቀዋል።  በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሚመራዉ የኢትዮጵያ መንግሥት በሃገሪቱ የዴሞክራሲ ግንባታን ከጀመረ ወዲህ ከኤርትራ አሁንም በርካታ ሰዎች እየተሰደዱ መሆኑን የጀርመን የዜና ወኪል «DPA» ዘግቦአል።   

 

አዜብ ታደሰ 

ተስፋለም ወልደየስ