1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጃፓን እና ቻይና ባለስልጣናት በኣፍሪካ

ረቡዕ፣ ጥር 7 2006

በተለምዶ እሩቅ ምስራቅ ተብሎ በሚታወቀው የኢሲያ ክ/ዓለም ከጃፓን ባህር በስተምስራቅ በሰላማዊ ውቅኖስ፣ በደሴት መልክ የምትገኘው ጃፓን ስያሜዋም እራሱ በእነርሱ ቐቐ አተረጉዋጎም የጸኃይ መነሻ እንደማለት ነው።

https://p.dw.com/p/1Ar4j
Shinzo Abe
ምስል DW/L. Matias

ትላልቆቹን ደሴቶች ማለትም ሆንሹ፣ ሆካይዶ፣ ኪይሹ እና ሺኮኩን ጨምሮ የ 6,852 ደሶቶች ስብስብ የሆነችው ጃፓን በህዝብ ብዛቷም በዓለማችን 10 ኛውን ደረጃ ይዛለች። 126 ሚሊየን ገደማ ህዝብ ኣላት።

ቀድሞ በትልቅነቱ በዓለማችን 2ኛ የሆነውን ግዙፍ ኢኮኖሚ በመገንባት የምትታወቀው ጃፓን በኣገር ውስጥ ጥቅል ምርትም ሆነ በገቢ እና ወጪ ሸቀጦች ደግሞ የ 4ኛነቱን ደረጃ እንደያዘች ትገኛለች። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ግን በግዙፍ ኢኮኖሚ ባለቤትነት የ 2ኛነቱን ደረጃ ለቃ ወደ 3ኛነት ዝቅ ለማለት ተገዳለች። በኣንጻሩ የአንበሳ ድርሻ ከያዘችው US አሜሪካ ለጥቃ በፈጣን እድገት እጅግ ግዙፍ ኢኮኖሚ በመገንባት የ2ኛነቱን ደረጃ የተቆናጠጠችው የጃፓኗ ጎረቤት ታላቐ ቻይና ናት። በኢኮኖሚዋ ግዝፈት 2ኛ ትሁን እንጂ ወደ ውጪ በምትልካቸው ሸቀጦች ግን ግንባር ቀደም ናት ቻይና። በቆዳ ስፋቷም ከሩሲያ ቀጥላ 2ኛ ስትሆን፣ በህዝብ ብዛቷ ግን ለማነጻጸር በሚቸግር ልዩነት ቀዳሚቱኑን ይዛ ትገኛለች። 1 ቢሊየን 350 ሚሊየን ህዝብ ኣላት። ከኣጠቃላዩ የኣፍሪካ ህዝብ በ 250 ሚሊዮን ይበልጣል።

የባህር ይዞታን ሳይጨምር 20,4 በመቶ የየብስ ስፋት በመያዝ የዓለማችን 2 ኛዋ ስፊ ኣህጉር ኣፍሪካ የህዝብ ብዛቷም 1,1 ቢሊየን ይገመታል። ከኣጠቃላይ ህዝቧ 54 በመቶ የሚሆነው በ19 ዓመት እድሜ ክልል ውስጥ የሚገኝ በመሆኑ ደግሞ The youngest contnent (ወጣቷ ክ/ዓለም) በመባልም ትታወቃለች። በተለያዩ በርካታ ምክኒያቶች በዓለማችን ለዘመናት ጥልቅ በሆነ ድህነት ብትታወቅም ታዲያ ያንኑ ያህል ደግሞ ይህ ነው የማይባል የተፈጥሮ ሀብትም እንዳላት ግልጽ ነው። ከዚሁ የተነሳ ኣህጉሪቱ በተለይ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የከበርቴዎቹን ኣገራት ትኩረት እየሳበች መምጣቷ ሲታወቅ ካሳለፍነው ሳምንት ማገባደጃ ኣንስቶ የጃፓን እና የቻይና ቱባ ቱባ ባለስልጣናት ያውም በተመሳሳይ ጊዜ ኣፍሪካን እየጎበኙ መሆናቸውም ይታወቃል።

China Präsident Xi Jinping Staatsbesuch Jakarta Indonesien
ምስል Reuters

የዛሬው የኢኮኖሚ ዝግጅታችንም በዚሁ ጉዳይ ላይ ያተኩራል፣ ከዝግጅቱ ጋር ጃፈር ዓሊ ነኝ መልካም ቆይታ።

የኣፍሪካ ጉብኝታቸውን ባለፈው ሰኞ በአዲስ ኣበባ ያጠናቀቁት የጃፓኑ ጠ/ሚ፣ ሺንዞ ኣቤ፣ ለተመሳሳይ ተልዕኮ ትላንት ወደ ኦማን ማምራታቸው ታውቐል።

በተመሳሳይ መልኩ የቻይናው የው/ጉ/ሚኒስትር ዋንግ ኪዪም ካሳለፍነው ሳምንት ጀምሮ ኢትዮጵያን ጨምሮ አራት የኣፍሪካ ኣገሮችን መጎብኘታቸው ሲታወቅ፣ የሁለቱ የኢኮኖሚ ባላንጣዎች ጎን ለጎን ኣፍሪካን መጎብኘታቸው በእርግጥ ለምን? ማሰኘቱ ኣልቀረም። ይህም፤ የኢኮኖሚ ባለሙያዎች እንደሚሉት በሁለቱ ኣገሮች መካከል ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተጋጋለ በመጣው የኢኮኖሚ ፉክክር ብቻም ሳይሆን፤ የሚያመለክተው፤ የኣህጉረ ኣፍሪካም ኣስፈላጊነቷ ያንኑ ያህል እየጎላ መምጣቱንም ጭምር ነው።

የቻይና ፈጣን ግስጋሴ ከጃፓንም ኣልፎ ምዕራባውያኑንም እያሳሰበ መምጣቱ በሚነገርበት በኣሁኑ ወቅት የኣንድ ኣገር እድገት ሌላውን የሚጎዳ ሆኖ ሳይሆን ነገር ግን ቻይና ጃፓንን ከዓለም ገበያ በተለይም ከኣፍሪካ እየገፋች መምጣቷ ነው ኣሳሳቢነቱ። የኣሁኑ የጠ/ሚ ኣቤ ተልዕኮም ከዚሁ የመነጨ ሲሆን በአግባቡ መጠቀም ከተቻለ ክስተቱ ለኣፍሪካም የጎላ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ይኖረዋል ተብሎ ይታመናል።

ቀድሞ በአዲስ ኣበባ ዩኒቨርሲቲ እና ከዚያም ወዲህ እዚህ በጀርመን ኣገር በመምህርነት ያገለገሉት ዶ/ር አለማየሁ ብሩ ሁኔታውን ያብራሩታል።

የጃፓኑ ጠ/ሚ ኢትዮጵያን በጎበኙበት ወቅት ለኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች የሚውል የ 10 ቢሊየን የን ብድር የፈቀዱ ሲሆን በተመሳሳይ ሁኔታ ለሞዛንቢክ 50 ሚሊየን የን ገደማ እና ለኣይቮሪኮስትም እንዲሁ ዳጎስ ያለ ገንዘብ መፍቀዳቸው ታውቐል።

AU Hauptsitz in Addis Abeba
ምስል Getty Images

በተመሳሳይ ሁኔታ ወደ ኣፍሪካ ያመሩት የቻይናው የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ኪዪም ኢትዮጵያን፣ ጂቡቲን፣ ጋናን እና ሰኔጋልን ጎብኝቷል። የው/ጉ/ሚ ኪዪ በዚህ ጉብኝታቸው ከኢትዮጵያው የው/ጉ/ሚ ቴዎድሮስ ኣድኃኖም፣ ከጂቡቲው ኣቻቸው መሀመድ አሊ፣ ከጋናው ሃናህ ቴቴህ እና ከሰኔጋሉ የው/ጉ/ሚ ማንኩዬር ኒዲያዬ በተጨማሪም ከየኣገሮቹ መሪዎች ጋርም መምከራቸው ታውቐል።

የቻይና የው/ጉ/ሚኒስትሮች እኣኣ ከ 1991 ወዲህ በየዓመቱ በዓመቱ መጀመሪያ ኣፍሪካን መጎብኘታቸው የተለመደሲሆን ከሳኃራ በታች ያሉ የኣፍሪካ ኣገሮችን ሲጎበኙ ግን የዋንግ ጉብኝት የመጀመሪያው መሆኑ ነው።

ጃፈር ዓሊ

ነጋሽ መሓመድ