የፕሬዝደንት ኢሳያስ መግለጫ እና አረና ትግራይ
ረቡዕ፣ ሰኔ 13 2010ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ መንግስት ተቃዋሚ ፓርቲ አረና ትግራይ፤ 20 ዓመት ያስቆጠረዉን የኢትዮ-ኤርትራን ጦርነት እና ዉዝግብ በሰላም ለማስወገድ የሁለቱ ሐገራት መንግሥታት የጀመሩትን መቀራረብ እንደሚደግፍ አስታዉቋል።ይሁንና የፓሪቲዉ ሊቀመንበር አቶ አብረሐ ደስታ እንዳሉት የሠላም ጥረቱም ሆነ ገቢራዊነቱ የግጭቱ ማዕከል የነበሩትን አካባቢዎች ሕዝብ ጥቅምን እንዳይጎዳ ጥንቃቄ ያስፈልገዋል።የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር የአረና ትግራይ ሊቀመንበር እና አንድ የአምደ መረብ ፀሐፊን አናጋግሮ የላከልንን ዘገባ እነሆ።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ነጋሽ መሐመድ
አዜብ ታደሰ