1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ያለአግባብ የጫኑትን ነዳጅ ደብቀዉ የነበሩ ከ50 በላይ መኪኖች በአፋር ክልል ተያዙ

ሰኞ፣ ታኅሣሥ 28 2017

በወሩ መጨረሻ ላይ የነዳጂ ዋጋ ክለሳ ይደረጋል በሚል ዕሳቤ በአፋር ክልል የተለያዮ ቦታዎች ነዳጅ ጭነዉ ተደብቀዉ የነበሩ ከ50 በላይ ቦቴ መኪኖች ከተደበቁበት መያዛቸዉን የአፋር ክልል ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ አስታዉቋል።

https://p.dw.com/p/4os0G
Dessie, Äthiopien | Schlangen von Autos für Treibstoff
ምስል Esayas Gelawe Ayalew/DW

ነዳጅ የደበቁ በርካታ ተሽከርካሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው

ያለአግባብ ነዳጅ  ደብቀዉ የነበሩ ከ50 በላይ ነጃጂ ጫኝ መኪኖች በአፋር ክልል ተያዙ

 

በወሩ መጨረሻ ላይ የነዳጂ ዋጋ ክለሳ ይደረጋል በሚል ዕሳቤ በአፋር ክልል የተለያዮ ቦታዎች ነዳጅ ጭነዉ ተደብቀዉ የነበሩ ከ50 በላይ ቦቴ መኪኖች ከተደበቁበት መያዛቸዉን የአፋር ክልል ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ አስታዉቋል የመምሪያዉ ኃላፊ አቶ አህመድ አብዱልቃድር በጋላፊ ፣ ዉሀ ልማት ፣ ዲሽኦቶ: ፣ ሰርዶና ሌሎች ቦታዎች ነዉ ወደሀገር ዉስጥ ከገቡ ቀናትን ያስቆጠሩ ነዳጂ ጫኝ መኪኖች ማያዛቸውን ተናግረዋል። 

የቤንዚን እጦት ፈተና የሆነባቸው የሀዋሳ ከተማ አሽከርካሪዎች

ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ የነዳጂ ጫኝ መኪናን ያሽከረከሩና ለስራቸዉ ደህንነት ሲባል ስማቸዉ እንዳይገለፅ የፈለጉ አስተያየት ሰጭ በጅቡቲ ነዳጂ ለመቅዳት በሚኖር ወረፋ ከአስር እስከ አስራአምስት ቀናትን በዚያ ብንቆይም የነዳጂ ጫኝ መኪና ያሏቸዉ ባለማድያዎች ግን በወሩ መጨረሻ ላይ ነጃጂ የጫኑ መኪኖቻቸዉ እንዲዘገዮ መፈለጋቸውን ገልጸዋል።

ነዳጂን ከጂብቲ በማስመጣት ለተጠቃሚዎች የሚያከፋፋሉት  የነዳጂ ማድያ ስራአስኪያጂ የሆኑት አቶ ታደለ በቀለ ችግሩ ባለማደያዎች ዋጋ ለመጨመር በሚያደርጉት ጥረት  ሳይሆን የአቅርቦት እጥረት በመኖሩ የተፈጠረ ነዉ ባይ ናቸው። 

በአዲስ አበባ ከተማ የመጓጓዣ ታሪፍ ጭማሪ እና የነዋሪው አቤቱታ

ከሰሞኑ በአፋር ክልል በነጃጂ ጫኝ ቦቴ መኪኖች ላይ እየተደረገ ያለዉ ክትትል እስከምንድረስ ነዉ ብለን የጠየቅናቸዉ የየክልሉ ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ አህመድ አብዱል ቃድር መኪኖቹ የደህንነት ስጋት ሳይገጥማቸዉ ከክልሉ እንዲወጡ የማድረግ ተግባር እንደሚሰሩ ጠቁመዋል። በቀጣይም ነዳጂ የጫኑ ቦቴ መኪኖች በአፋር ክልል ተደብቀዉ እንዳይቆዮ ከተለያዮ የፀጥታ መዋቅር ጋር በመሆን ይሰራል ተብሏል።

ኢሳያስ ገላው

ታምራት ዲንሳ 

እሸቴ በቀለ