1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ያለፈው አንድ ዓመት በአዲስ አበባ ነዋሪዎች ዓይን

ረቡዕ፣ መጋቢት 25 2011

አንድ ዓመት ባስቆጠረው የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የሥልጣን ዘመን በርካታ አዎንታዊ ውጤቶች የመመዝገባቸውን ያህል ችግሮች እና ተግዳሮቶችም አልታጡም። ስለ አንድ ዓመቱ የለውጥ ሂደት የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ምን ይላሉ? DW ዶቼቬለ አስተያየቶች አሰባስቧል። 

https://p.dw.com/p/3GBsx
Äthiopien Addis Abeba
ምስል DW/S. Muchie

በለውጡ ሂደት ላይ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ምን ይላሉ?

አንድ ዓመት ባስቆጠረው የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የሥልጣን ዘመን በርካታ አዎንታዊ ውጤቶች የመመዝገባቸውን ያህል ችግሮች እና ተግዳሮቶችም አልታጡም። በሺዎች የሚቆጠሩ የፖለቲካ እስረኞች መፈታት፣ የፖለቲካ ምህዳሩ አካታች መሆን፣ በምህረት አዋጅም ብዙዎች ወደ ሀገራቸው መመለስ መቻላቸው፣ በኤርትራ እና በኢትዮጵያ መካከል ሰላም መውረዱ ከለውጡ ዋና ዋና ውጤቶች ውስጥ ይጠቀሳሉ። በአንጻሩ በዚህ አንድ ዓመት በሰላም እጦት ሰዎች መሞት መፈናቀላቸው በአንዳንድ አካባቢዎችም ሥራ እና ትምሕርት መስተጓጎሉ በአሉታዊ ጎኑ ይነሳል። ስለ አንድ ዓመቱ የለውጥ ሂደት የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ምን ይላሉ? DW ዶቼቬለ የሚከተሉትን አስተያየቶች አሰባስቧል። 
ጌታቸው ተድላ /ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሄር
ነጋሽ መሐመድ 
ሸዋዬ ለገሠ