ገጣሚ በቀለ ወያ ፍርድ ቤት ሳይቀርብ 4 ወር ሞላው
ቅዳሜ፣ ታኅሣሥ 6 2016ገጣሚ በላይ በቀለ ወያ በፀጥታ ኃይሎች ተይዞ በእሥር ላይ ከሆነ አራት ወራቶች እንደሞሉት ጠበቃው ተናገሩ።
ጠበቃው ለዶቼ ቬለ እንዳሉት በላይ በቀለ በአማራ ክልል በተደነገገው የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ምክንያት መታሰሩንና በቅርቡ ባህር ዳር ከተማ ታስሮ እንደሚገኝ መስማታቸውን ገልፀዋል።
በትናንትናው እለት ሁኔታውን በተመለከተ እቤቱታ ለማስገባት ቤተሰቦቹ ወደ ፍትሕ ሚኒስቴር ደብዳቤ ለማስገባት ሄደው እንደነበር የገለፁት ጠበቃ ብሩክ ደረጄ ይሁንና ፍትሕ ሚኒስቴር አቤቱታቸውን እንዳልተቀበለ ገልፀዋል።
ገጣሚ በላይ በቀለ ወያ
ገጣሚ በላይ በቀለ ወያ ባለፈው ዓመትም የት እንደታሠረ በማይታወቅበት ሁኔታ ለሳምንታት ታሤስሮ ቆይቶ መለቀቁ ይታወሳል። በላይ ወንጀል ሰርቶ እንደሆn ፍርድ ቤት ቀርቦ ፍርድ ማግኘት ነበረበት ያሉት ጠበቃው ነገር ግን ያለፍርድ በእስር ማቆየት ተገቢ አለመሆኑን ገልጸዋል። ከዚህ በተጨማሪ በላይ ታስሮ የሚገኘው ከጠያቂ እና ዘመድ ርቆ ባህርዳር ውስጥ መሆኑን እና ይህ ለእርሱ ነገሮችን አስቸጋሪ እንዳደረጉበት ተናግረዋል። ቤተዘመድ ወደሚገኝበት አዲስ አበባ እንዲመጣ እና ጉዳዩን መከታታል እንዲችልም ጠበቃው ጠይቀዋል።
በሌላ በኩል ከአንድ ወር በፊት አዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ላይ በተደረገው 23 ኛው ዙር የታላቁ ሩጫ ውድድር ላይ "በከተማው ኹከት እና ብጥብጥ ለመፍጠር አስባችኋል" እና "ፖለቲካዊ ይዘት ያለው ንግግር አድርጋችኋል" በሚል የታሰሩ ሰዎች ቁጥር 24 መድረሱን ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉት ጠበቃ ሰለሞን ገዛኸኝ ተናግረዋል።
ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በተከናወነበት ባለፈው ወር የሩጫ ተሳታፊ የነበሩ በደርዘን የሚቆጠሩ ወጣቶች በጸጥታ ኃይሎች ቁጥጥር ስር መዋላቸው ተዘግቦ ነበር ።
ሰለሞን ሙጬ
ታምራት ዲንሳ