1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጠ/ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ና ኤርትራ

ሐሙስ፣ ኅዳር 27 2005

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ከኤርትራ ጋር መወያየት እንደሚፈልጉ አስታወቁ። አቶ ኃይለማርያም ፣ የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊም የኢትዮጵያና የኤርትራ የድንበር ውዝግብ በድርድር እንዲፈታ በተለያዩ ጊዜያት መጠየቃቸውን አስታውሰዋል ።

https://p.dw.com/p/16wpw
Ethiopian state television announced on August 21, 2012 that Hailemariam Desalegn will be acting prime minister, after the death of Ethiopian Prime Minister Meles Zenawi.
ምስል CC-BY-SA- World Economic Forum

ኢትዮጵያ ከኤርትራ ጋር ውይይት ለማካሄድ እንደምትፈልግ አስታወቀች ። የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ከኤርትራ ጋር መወያየት እንደሚፈልጉ ለአልጀዚራ ጣቢያ በሰጡትና የፊታችን ቅዳሜ በሚተላለፍ ቃለ ምልልስ ላይ መናገራቸው በተለያዩ ድረ ገፆች ላይ ተዘግቧል ። አቶ ኃይለማርያም ፣ የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊም የኢትዮጵያና የኤርትራ የድንበር ውዝግብ በድርድር እንዲፈታ በተለያዩ ጊዜያት መጠየቃቸውን አስታውሰዋል ። ኢትዮጵያ ከኤርትራ ጋራ ማካሄድ ስለምትፈልገው ውይይት የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ ዲና ሙፍቲን አነጋግረናል ።  ኢትዮጵያ ከኤርትራ ጋር ማካሄድ እፈልጋለሁ ስላለችው ውይይት የኤርትራን መንግሥት አስተያየት ለማግኘት ሞክረን አልተሳካም።

ሂሩት መለሰ

ሸዋዮ ለገሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ