ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሖሳዕና
እሑድ፣ መስከረም 11 2012ማስታወቂያ
ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ በዛሬው ዕለት ወደ ሖሳዕና አቅንተው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል። በውይይታቸው ከተነሱላቸው ጥያቄዎች መካከል በዞኑ ነዋሪዎች የሚነሳው የክልል አደረጃጀት ጉዳይ፤ የሥራ አጥነት እና የወጣቶች ፍልሰት እና የኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ እጣ-ፈንታን የተመለከቱ ጉዳዮች ይገኙበታል።
ኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ በኢትዮጵያ እና በኤርትራ ጦርነት ወቅት የሚያበሩት ተዋጊ የጦር አውሮፕላን ተመቶ ከወደቀ በኋላ በኤርትራ እጅ የገቡት ከ21 አመታት ገደማ በፊት ነበር። ኮሎኔሉ እስካሁን በሕይወት ስለመኖራቸው ግልፅ ያለ ማረጋገጫ ከኤርትራም ይሁን ከኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ወገን አልተገኘም።
ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሖሳዕና በነበራቸው ቆይታ የኮሎኔል በዛብሕ ጴጥሮስ ጉዳይ የኢትዮጵያ እና የኤርትራ መሪዎች ስምምነት አንድ አካል እንደሆነ መናገራቸውን በውይይቱ የተሳተፉት የሐዲያ ዞን አስተዳደር የፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ካሳሁን አባይነሕ ለዶይቼ ቬለ አረጋግጠዋል።
ሸዋንግዛው ወጋየሁ
እሸቴ በቀለ