1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በኮምቦልቻ መድሀኒት በስርቆት ለግል መድሃኒት ቤቶች እየተሸጠ ነው ተባለ

ኢሳያስ ገላው
ሐሙስ፣ ጥር 1 2017

በእርዳታ የተገኙ መድሀኒቶች ከመንግስት ጤና ተቋማት ተዘርፎ ለግል መድሃኒት ቤቶች እየተሸጠ መሆኑን የኢትዮጵያ የምግብ እና የመድሃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን የኮምቦልቻ ቅርንጫፍ አስታውቋል። ዝርፊያዉ ከአንድ ክልል ወደ ሌላዉ ክልል ጭምር የሚከወን ነው ተብሏል።

https://p.dw.com/p/4oyxy
Pillen
ምስል Bilderbox

በኮምቦልቻ መድሀኒት በስርቆት ለግል መድሃኒት ቤቶች እየተሸጠ ነው ተባለ

በእርዳታ የገቡ  መድሀኒቶች በስርቆት ከመንግስት የጤና ተቋማት ወደ ግል የመድኃኒት መድሃኒት ቤቶች  እየተዛወሩ መሆኑን በኢትዮጵያና የምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ አስታወቀ ። ለመንግስት የህክምና ተቋማት ለሚያገለግሏቸዉ የማህበረሰብ ክፍሎች ህክምና ይዉል ዘንድ በኢትዮጵያ መድኃኒት አቅርቦት ኤጀንሲ በኩል በተለያዮ ግብረሰናይ ድርጂቶች ድጋፍ የሚገኙ መድኃኒቶች በማን እንዴትና መች እንደተሸጡ ሳይታወቅ በግል የመድኃኒት መሸጫ መደብሮች ሲሸጡ መመልከት እየጨመረ እንደመጣ በግል የመድኃኒት መደብር ተቀጥረዉ የሚሰሩ የፋርማሲ ባለሙያ ይናገራሉ።
ባለሙያዉ እንደሚገልፁት በመንግስት ህክምና ተቋማትየሚፈለጉና እጥረት አለባቸዉ ተብለዉ የሚታሰቡ መድኃኒቶች በስርቆት በሦስተኛ ወገን አልያም በመንግስት የህክምና ተቋም የሚሰራ ግለሰብ በቀጥታ ለሽያጭ ያቀርቧቸዋል መድኃኒቶቹ በእርዳታ የሚመጡም ናቸዉ ይላሉ።


መድኃኒቶቹ በመንግስት የህክምና ተቋማቶቹ መገኝት ያለባቸው ናቸው

የኢትዮጵያ መድኃኒትና ምግብ ቁጥጥር ባለስልጣን ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ አፋር ክልልን ጨምሮ ከደብረ ብርሀን አስከ ሰቆጣ ያለዉን አካባቢ የመድኃኒት ቁጥጥርን ይከታተላል  የቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ጁሀር አበጋዝም በእርዳታ የገቡና  ከመንግስት የህክምና ተቋም ዉጭ  ሊያዙ የማይገባቸዉ መድኃኒቶች በስርቆት ምክኒያት በግለሰብ ተቋም ይገኛሉ ብለዋል

አቶ ጁሀር መንግስት በነፃ የሚያመጣቸዉ የወባ መድኃኒቶች ምን ያህል ወደ ህክምና ተቋማቶቹ እንደገብና ጥቅም ላይ የዋሉትን የመለየት ስራ በአፋርና በኮምቦልቻ ከተማ ባሉ 9 የጤና ተቋማት ላይ  ክትትል ሲሰራ ተቋማቱ ጉድለት ተገኝቶባቸዋል መድኃኒቱ ተሰርቆ አልያም ለታማሚ ተሰጥተዋል ተብለዉ ይወጣሉ ብለዋል።

የኢትዮጵያ የመድሃኒት አቅራቢ ኤጄንሲ ባህርዳር ቅርንጫፍ
የኢትዮጵያ የመድሃኒት አቅራቢ ኤጄንሲ ባህርዳር ቅርንጫፍምስል Alemnew Mekonnen/DW

ስርቆቱ ከአንድ ክልል ወደ ሌላ ክልል 

አሁን ላይ መድኃኒትን ከመንግስት የህክምና ተቋማት በስርቆት የሚያወጡ  ግለሠቦችን ለመያዝ ጥረት ሲጀመር ዝርፊያዉ መልኩን በመቀየር ከአንድ ክልል ወደ ሌላዉ ክልል የሚከወን ሆኗል ይላሉ አቶ ጁሀር አበጋዝ «አሁን ደግሞ ስርቆቱ በሚታወቅበት ጊዜ ከአንድ ክልል ወደ ሌላ ክልል የማሻገር ከትግራይ ክልል ወደ አማራ ክልል ከአፋር ክልል ወደ ትግራይ ክልል መድኃኒቶቹን ይቀባበሏቸዋል።» በማለት ይናገራሉ።በኢትዮጵያ መድኃኒትና ምግብ ቁጥጥር ባለስልጣን የኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ሀላፊ።

ምንጫቸው ያልታወቁ መድኃኒቶችም ተገኝተዋል

ከመንግስት የህክምና ተቋማት ወጥተዉ በግል የመድኃኒት መሸጫ  መደብር መድኃኒት በብዛት የሚገኝባቸዉ እንደ ደሴ ከተማ ያሉ ከተሟችም ቁጥጥር መጀመራቸዉን የደሴ ከተማ ጤና መምሪያ ምክትል ኃላፊ አቶ ፍስሀ ዳዉድ ገልፀዋ በመንግስት ጤና ተቋም ብቻ መያዝ የሚገባቸዉ ያለባቸዉና በኮንትሮባንድ የገብ ምንጫቸዉ ያልታወቁ መድኃኒቶችን የመቆጣጠር ተግባር እየፈፀምን ነዉ ብለዋል

በእርዳታ የመጡ መድኃኒቶች በሽያጭ መቅረብ የለባቸዉም የሚሉት የኢትዮጵያ መድኃኒትና ምግብ ቁጥጥር ባለስልጣን ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ  ኃላፊ አቶ ጁሀር አበጋዝ ናቸዉ በእርዳታ የመጡ መድኃኒቶች አይሸጡም ለመንግስት ጤና ተቋማትመንግስት በነፃ የሰጣቸዉ ናቸዉ መድኃኒቶችን መያዝም አይቻልም ይላሉ

እነኝህ በእርዳታ የቀረቡ መድኃኒቶች ያለ ደረሰኝ የሚሸጡና ቁጥጥር  የማይደረግባቸዉ ናቸዉ የሚሉት የፋርማሲ ባለሙያ መድኃኒቶቹ ያለ ደረሰኝ የሚሸጡ ሲሆን ደረሰኝ የሚፈልግ ገዥ ካለም ስማቸዉ ተቀይሮ ይቆረጥላቸዋል የመድኃኒት ቁጥጥር የሚከዉኑ ባለሙያዎች ሲመጡም ቀድሞ መረጃ ስለሚደርሳቸዉ መድኃኒት የመሰወር ተግባር ይሰራል ይላሉ

የኢትዮጵያ መድኃኒትና ምግብ ቁጥጥር ባለስልጣን ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ  በእርዳታ ለመንግስት የህክምና ተቋማት የሚሰጡ መድኃኒቶች ልዮ መለያ ተሰርቶላቸዉ በኢትዮጵያ መድኃኒት አቅርቦት ኤጀንሲ በኩል እንዲቀርቡ እየተሰራም ነዉ ብሏል።

 

ኢሳያስ ገላው
እሸቴ በቀለ
ፀሀይ ጫኔ