1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ፖለቲካእስያ

የሳውዲ ተመላሾች አዲስ አበባ ገቡ

ዓርብ፣ ሚያዝያ 4 2016

በሳዑዲ ዓረቢያ በእሥር ቤት እና በተለያየ ፈታኝ ሁኔታ ውስጥ ከሚገኙት ኢትዮጵያውያን መካከል የተወሰኑት ዛሬ በኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን አዲስ አበባ ገቡ ። መንግስት ጥረት 70 ሺህ ኢትዮጵያውያንን የማስመለስ ውጥን እንዳለው ዐሳውቋል ።

https://p.dw.com/p/4ehY7
Rückkehr Äthiopier aus Saudi-Arabien nach Addis Abeba
ምስል Solomon Muchie/DW

በሳዑዲ እሥር ቤቶች ኢትዮጵያውያን እንደሚሰቃዩ ይነገራል

በሳዑዲ ዓረቢያ በእሥር ቤት እና በተለያየ ፈታኝ ሁኔታ ውስጥ ከሚገኙት ኢትዮጵያውያን መካከል የተወሰኑት ዛሬ በኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን አዲስ አበባ ገቡ ። መንግሥት 70 ሺህ የሚሆኑ ዜጎችን ወደ ሀገራቸው ለማስመለስ ብሔራዊ ኮሚቴ አቋቁሞ ሰሞኑን ከሳውዲ አረቢያ መንግሥት ባለስልጣናት ጋር የተነጋገረ ሲሆን፤ ከዛሬ ጀምሮ በሣምንት 12 በረራዎችን በማድረግ በሚቀጥሉት አራት ወራት ዜጎችን ማስመለሱን እንደሚቀጥል ዐስታውቋል ። ሳውዲ አረቢያ ውስጥ በተለያየ ወንጀል ተጠርጥረውና ተፈርዶባቸው በእሥር ቆይተው የፍርድ ጊዜያቸውን ያጠናቀቁ ኢትዮጵያውያን ወደ ኢትዮጵያ ባለመመለሳቸው ለሌላ እሥር ተዳርገው በችግር መሆናቸውን ከዚህ በፊት ደጋግመው አቤት ብለው ነበር ። በዛሬው እለት በሁለት በረራዎች በማድረግ 842 ኢትዮጵያውያንን ማስመለሱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል ። 

ዜጎችን የማስምለስ ጥረት

ሰሞኑን ከሳውዲ አረቢያ መንግሥት ባለሥልጣናት ጋር ምክክር ያደረገው የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ቡድን ከዛሬ ጀምሮ ሳውዲ አረቢያ ውስጥ ሪያድ እና ጅዳ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞችን ማስመለስ ጀምሯል። ዛሬ የተመለሰቱ አብዛኞቹ ወጣት ወንዶች ናቸው። ለሁለተኛ ጊዜ በዚሁ ሁኔታ ሳውዲ አረቢያ መሄዱን የነገረን ወጣት ከአንድ ዓመት በላይ በታሰረበት ወቅት ለበሽታ እና ለችግር መጋለጡን ይገልፃል።

ይሄው ወጣት ሀገር ሰላም ብትሆን ማንም ተመልሶ ወደ ችግር ቦታ አይሄድም ሲሉም ተመልሶ የሄደበትን ምክንያት ያስረዳል። ሳውዲ አረቢያ ውስጥ በተለያየ ወንጀል ተጠርጥረውና ተፈርዶባቸው በእሥር ቆይተው የፍርድ ጊዜያቸውን ያጠናቀቁ ኢትዮጵያውያን ወደ ኢትዮጵያ ባለመመለሳቸው  ለሌላ እሥር ተዳርገው በችግር ላይ እንደሚገኙ  ከዚህ በፊት ደጋግመው ገልፀዋል። አሁንም እዚያው ለቀሩት መንግሥት እንዲደርስላቸው ጠይቀዋል።

70 ሺህ ኢትዮጵያውያንን የማስመለስ ውጥን እንዳለው መንግሥት ዐስታውቋል
70 ሺህ ኢትዮጵያውያንን የማስመለስ ውጥን እንዳለው መንግሥት ዐስታውቋል ምስል Solomon Muchie/DW

በርካታ ኢትዮጵያውያን ለስደት የሚመርጧት ሳውዲ አረቢያ

በሳውዲ አረቢያ በችግር ውስጥ ይኖሩ የነበሩ ዜጎችን  ወደ ሀገራቸው ለማስመለስ የተያዘው የመንግሥት የአንድ ዓመት  እቅድ 131 ሺህ ዜጎችን በማስመለስ ባለፈው ዓመት ተጠናቋል።

አሁን በተጀመረው ዜጎችን ጥረት 70 ሺህ ኢትዮጵያውያንን የማስመለስ ውጥን እንዳለው መንግሥት ዐስታውቋል ።

ሰለሞን ሙጬ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ሸዋዬ ለገሠ