የርዕሠ-ብሔር ሣኅለወርቅ ዘውዴ የሁለቱ ም/ቤቶች የመክፈቻ ንግግር
ሰኞ፣ መስከረም 28 2016«ጦርነት አማራጭ ሆኖ መቅረብ የለበትም» ርዕሠ ብሔር ሣኅለ ወርቅ ዘውዴ
የሕግ የበላይነትን ማረጋገጥ እና የሰላም መንገዶችን አሟጦ መጠቀም እንዲሁም ዘላቂ ሀገራዊ ሰላምን ለማረጋገጥ መሥራት የዚህ ዓመት የመንግሥት ዋና ተግባር መሆኑን የኢትዮጵያ ርዕሠ ብሔር ሣኅለ ወርቅ ዘውዴ አስታወቁ ። የፌደሬሽን እና የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤቶችን የ2016 የጋራ ጉባኤ ዛሬ ከቀትር በኋላ ሲከፍቱ "ጦርነት አማራጭ ሆኖ መቅረብ የለበትም" ያሉት ፕሬዝዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ፣ መንግሥት ከማንኛውም ኃይል ጋር ለመነጋገር ዝግጁ መሆኑን ጠቅሰዋል። ርዕሰ-ብሔሯ የሰላም እና የእንድነት ጥሪ አቅርበዋል። በየትኛውም አካባቢ ያሉ ግጭቶች በሠላም እንዲፈቱም ጠይቀዋል። ለዚህም የተጀመረው የሀገራዊ ምክክር ሥራ ትልቅ ተስፋ ያለው ጅምር የፖለቲካ ተግባር መሆኑን ገልጸዋል። አዲሷ ፕሬዚደንት እና የሐረር ድምጾች
ርዕሠ ብሔር ሣኅለወርቅ ዘውዴ ያነሷቸው አንኳር ጉዳዮች
የመንግሥትን 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሲከፍቱ ኢትዮጵያ ባለ ሁለት መልክ መሆኗን በመግለጽ ለ40 ደቂቃ ቆመው ንግግራቸውን ያሰሙት የኢፌዴሪ ርዕሠ ብሔር ሣኅለወርቅ ዘውዴ ኢትዮጵያ ጥንታዊት ከመሆኗ ባሻገር ለዓለም በታሪክ፣ በጥበብ፣ በአርበኝነት በአሰባሳቢነት ጉልህ ድርሻ ያበረከተች ሆና ሳለ በሌላ በኩል በአሁኑ ወቅት ራሷን በሚያቀጭጭ እና በሚያወድም ችግር ውስጥ መሆናን አብራርተዋል። ትናንት ለነገ እንቅፋት መሆን የለበትም ያሉት ፕሬዝዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ ተጀምራል ያሉት አዲስ የብልጽግና ምዕራፍ ዘላቂ እንዲሆን ለሀሳብ እና ውይይት ቅድሚያ እንዲሰጥ ማድረግ ይገባል ብለዋል።
"ሁላችንንም ሊያግባባ የሚችል ሀገራዊ ትምምን መፍጠር አቅቶናል። ሁላችንንም ሊያሰባስብ የሚችል ትርክት መገንባት ተስኖናል"። በሰሜን ተቀስቅሶ ከፍተኛ ውድመት ያስከተለው ጦርነት በሰላም በውይይት የመቋጨቱ በመንግሥት ትምህርት የሚወሰድበት መሆኑንም ገልፀዋል። ይሁንና እድሎች በእጅ እያሉ የማምከን እና በዋዛ የማሳለፍ በጎ ያልሆነ ልማድ መኖሩን በማስታወስ በየትኛውም አካባቢ ያሉ ግጭቶች በሰላም እንዲፈቱ መንግሥት ፍላጎቱ መሆኑንና ለዚህም የሀገራዊ ምክክሩ ትልቅ ትፕስፋ ያለው ሀገራዊ ተግባር መሆኑን አበክረው ገልፀዋል። በወቅታዊ ጉዳዮች የው/ጉ ሚኒስቴር መግለጫ
ድህነትና ኋላ ቀርነት ኢትዮጵያ ከፊት የወረሰቻቸው ችግሮች መሆናቸውን ፣ መንግሥት እነዚህን ፈታኝ ሁኔታዎች ለማስወገድ ጥረት እያደረጉ የሚቀጥል መሆኑን አብራርተዋል። ፀጥታ ችግር፣ የኑሮ ውድነት ፣ ሌብነትና ሙስና ፣ ሕገወጥ ንግድ እና ብልሹ አሰራር ፈታኝ ችግሮች ናቸው ያለት ርዕሠ ብሔር ሣኅለወርቅ ዘውዴ በዚህ ዓመት መንግሥት ሕግ የማስካበር ሥራ ላይ ትከረት ያደርጋል ብለዋል።
የሕዝብን አንድነት የሚሸረሽር ችግር ተበራክቷል
ርዕእሠ-ብሔር ሣኅለወርቅ ዘውዴ በዚሁ የዛሬው የሁለቱ ምክር ቤቶች የመክፈቻ ንግግራቸው የሕዝብን አብሮ የመኖር ልማድ፣ እህትማማችነትና አንድነትን ለማላላትና ለመበጠስ የሚደረግ ዘመቻ እየተበራከተ መጥቷል ብለዋል። ይህ የህዝብን እንድነት እንዳይሸረሽር ሥጋት እንዳለም ገልፀዋል። ለምክንያታዊ የፖለቲካ ሥራ ትከረት ይደረጋል ያለት ፕሬዝዳንቷ ኢትዮጵያ ታላቅ ሀገር መሆኗንና ይህ ታላቅነቷ በሚመጥን መልኩ ለዓለም መገለጥ እንዳለባት አውስተዋል።ከነጠላ ቡድናዊ ፍላጎት ወጥተን ሀገራዊና ገዢ ያሉት "ብሔራዊነት" እንዲቀነቀንም ጥሪ አድርገዋል።
ኢትዮጵያ በችግር ውስጥ ሆናም ቢሆን እድገት አስመዝግባለች ፣ ሆኖም ኢኮኖሚዋ አዲስ የታሪክ እጥፋት ላይ ነው ሲሉ ያብራሩት ፕሬዝዳንቷ ኢትዮጵያ ብሪክስ ይባል የነበረው ስብስብ አባል እንድትሆን የትጀመረው ሥራ የመንግሥት የዲፕሎማሲ ስኬት ጉልህ ማሳያ አድርገው ጠቅሰውታል።የኢትዮጵያ ታላቁ ሕዳሴ ግድብ የሲቪል ግንባታ ሥራ በዚህ ዓመት ሙሉ በሙሉ ይጠናቀቃል የሚል ግምት ምኖሩንም በመጥቀስ ሁሉም የምትታነጽ፣ በእኩልነት ለሁሉም የምትሆን ኢትዮጵያ እንድትገነባ ርብርብ እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል።
ሰሎሞን ሙጬ
ኂሩት መለሰ
እሸቴ በቀለ